Thursday 31 October 2013

Ethiopian Orthodox Mezmur-Be Werke Kelem Tesifeshal - Zemarit Tsigereda


Ethiopian Orthodox Tewahedo Mezmur - Kidist Arsema - Zemarit Tsegereda Tilahun


Zemari Yilma Hailu - Zim atbelu



Zemari Yilma Hailu - Besew zend bimuatet tesfana desta...


Ethiopian Orthodox Mezmur - Yeab kal Akbrosh - Yilma Hailu - የአብ ቃል አክብሮሽ

New Ethiopian orthodox mezmur Yilma Hailu Selam Le ki

ወበዛቲ ዕለት

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

ጥቅምት 22 ... ዕረፍቱ ለቅዱስ ሉቃስ ወንጌላዊ 

በዚህች ቀን ወንጌላዊው ቅዱስ ሉቃስ ዐረፈ:: የሉቃስ ወንጌልንና የሐዋርያት ሥራን የጻፈልን አባት ነው:: 
ቁጥሩ ከ 72ቱ አርድዕት ነው፤ቀድሞ ዶክተር ነበር መድሐኒት ቀምሞ የሥጋ በሽታን የሚፈውስ በኋላ ግን
ወንጌልን ሰብኮ የነፍስን ቁስልን የሚፈውስ ሆኗል::

ወንጌሉን መቼ ጻፈው? ቢሉ ጌታ ባረገ በ 22 ዓመቱ የት ጻፈው?መቄዶኒያ በምን ቋንቋ? በዮናኒ፤ማቴዎስ

በዕብራይስጥ፤ ማርቆስ በሮማይስጥ፤ ዮሐንስ በጽርዕ ቋንቋ ነው የጻፉት። ቅዱስ ሉቃስ መጀመሪያ ዮሐንስን
ተከትሎ ወንጌል ሰበከ በኋላም ከቅዱስ ጳውሎስ ጋር ሮም ሲሰብኩ ቅዱስ ጳውሎስ በኔሮን እጅ በሰማዕትነት
ዐረፈ፤ ብቻውን እየተዘዋወረ ወንጌለ መንግሥተ ሰማያትን ሰበከ::

የክርስቲያኖች ቁጥር በዛ አብያተ ጣኦታትንም አፈራረሰ በዚህም ንጉሱ ተቆጣ ሸንጎ ፊት አቅርቦም፤ ወንጌልን

የጻፈች እጅህ ይህች ነችን? ብሎ ቀኝ እጁን ቆረጠው፤ ቅዱስ ሉቃስም "ኢየሱስ ክርስቶስ የተቆረጠ እጅ
አይደለም የተቆረጠች ነፍስንም ይቀጥላል::" ብሎ በግራ እጁ የተቆረጠች እጁን አንስቶ እንደ ቀድሞ አደረጋት፤
በወንጌል ላይ ጌታችን የተቆረጠች የማልኮስን ጆሮ ወደ ቀደመ ቦታዋ እንደ መለሳት ልብ ይሏል፤ "በእኔ የሚያምን
እኔ የማደርገውን ያደርጋል ከኔም በላይ ያደርጋል::" ያለ ጌታ የታመነ ነው። ቅዱስ ሉቃስ ያደረገውን ተአምር
ተመልክተው 267 ወታደሮችና መኮንኑ በክርስቶስ አምነዋል፤ ንጉሱም በሰይፍ አስፈጅቷቸዋል፤ ቅዱስ ሉቃስንም
ጥቅምት 22 ቀን አንገቱን ቆርጦ በአሸዋ ከተሞላ ስልቻ ጋር አድርገው ወደ ባሕር ጥለውታል::

"... ምስለ ኤጲስቆጶስ ያዕቆብ ዘኢየሩሳሌም
ይምጽኡ ኀቤነ ለባርኮትነ ዮም
ማርቆስ ዘኣንበሳ ወሉቃስ ዘላሕም።"

ከሐዋርያው በረከት ያሳትፈን፤  አሜን! አሜን! 
አሜን!

Tuesday 29 October 2013

ወበዛቲ ዕለት

ጥቅምት 20 በዚህች ቀን አባ ዮሐንስ ሐጺር አረፈ፤ ቁመቱ አጭር ስለሆነ ነው ዮሐንስ ሐጺር የተባለው፤
በ18 ዓመቱ በገዳመ አስቄጥስ መንኩሶ በተጋድሎ ኖረ፤ ይህ አባት ነጽሮተ ስሉስ ቅዱስ የደረሰ አባት ነው፤
እዚህ ደረጃ የደረሱ አባቶች ቀና ቢሉ ሥላሴን ይመለከታሉ ዝቅ ቢሉ እንጦሮጦስን ያያሉ፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን 
የገዳሙ አብምኔት ሊፈትነው ብሎ ደረቅ እንጨት ሰጠው ይህንን ተክለህ አለምልመህ ፍሬውን አምጣልኝ አለው፤
እርሱም እንጨቱን ተከለው 3 ዓመት ሙሉ ከሩቅ ቦታ ውሃ እየቀዳ አጠጣው በ3ኛው ዓመት ጸደቀ ለመለመ ትልቅ 
ዛፍም ሆነ፤ ፍሬም አፈራ፤ መነኮሳቱ ይህ የትእግስት ውጤት ነው ብለው ፍሬውን ቀምሰውለታል፡፡ አንዲት አትናስያ 
የምትባል ሴት ነበረች፤ መጀመሪያ ጻድቅ ነበረች በኋላ ላይ በዝሙት ወደቀች ዘማዊም ሆነች፤ የቀድሞ ቅድስናዋን 
የሚያውቁ መነኮሳት ሊመክሯት ቢመጡ ሳቀችባቸው አሁን ማንን እንላክ ብለው አሰቡ ዮሐንስ ሐጺርን ላኩት፤ 
ተራ ሰው መስሎ ገባ፤ ለዝሙት የመጣ መስሏት ተቀበለችው፤ተጫወት አለችው ዮሐንስ ሐጺር ማልቀስ ጀመረ 
ምን ያስለቅስሃል ትለዋለች መልክሽ ደስ ብሎኝ ይላታል፤ደስ የሚል መልክ ያስቃል እንጂ መች ያስለቅሳል ትለዋለች 
የለም ነገ ገሃነም እንደምትወርጂ ታይቶኝ ነው አንድም ብዙ አጋንንት በሰውነትሽ ሲወጡ ሲወርዱ አያለሁ አላት፤ 
ደነገጠች ምን ይሻለኛል ትለዋለች፤ ንስሃ ገቢ ማን ያስታርቀኛል ኃጢአቴ ብዙ ነው ትለዋለች፤እኔ አስታርቅሻለሁ 
ተከተይኝ ብሎ ወጣ ልዋል ልደር ሳትል በሯን እንደተከፈተ ተከተለችው በልስላሴ የኖረ እግር ተበጣጥሶ በበዙ ደካም 
ሲመሽ ከገዳሙ ደረሱ፤የምታርፍበትን ቦታ ለይቶ ሰጣት፤ ሌሊት ለጸሎት ሲነሳ መላእክት ሲወጡ ሲወርዱ ያያል፤ 
ምንድን ነው ብሎ አንዱን መልአክ ይጠይቀዋል፤ትላንትና አንተን ተከትላ የመጣችው ሴት አርፋ ነፍሷን እያሳረግን
ነው ይለዋል፤ እግዚኦ ንስሃ ሳትገባ ብሎ ይደነግጣል፤ አንተን ልትከተል ገና አንድ እግሯን ከቤት ስታወጣ ኃጢያቷ
በሙሉ ተፍቆላታል፤ አሁን ወደ ገነት እየወሰድናት ነው ይለዋል፤ዮሐንስ ተገረመ፤የመቃብሯስ ነገር አለው፤ 
አንበሶች ይመጣሉ ቦታውን ለካላቸው ይለዋል፤አንበሶች ቆፍረውለት ቀብሯታል፤ ዮሐንስ ሐጺር በተጋድሎ ኖሮ
ጥቅምት 20 ዕለት አርፏል፤ በረከቱ ይደርብን፡፡


Monday 14 October 2013

ወበዛቲ እለት

ጥቅምት 4 
በዚህች ቀን የኢትዮጵያ ባለውለታዎች፤ ኢትዮጵያን ኢትዮጵያ እንድትሆን ትልቁን ድርሻ ያበረከቱ አብርሃና አፅብሃ የእረፍት ቀናቸው ነው፤እነዚህ ሁለት ጻድቅ ነገስታት ወንድማማች ሲሆኑ የክርስትና እምነትን በኢትዮጽያ ያበሩ አማናዊ ጥምቀትንና ቁርባን ያስጀመሩ ከመሆናቸው ባሻገር ከ 154 በላይ አብያተክርቲያናት አንጸዋል፤ ከነዚህም በተለይ ዋንኞቹ ትግራይ ውስጥ ገልአርታ ቀመር አርብአቱ እንስሳ፤ጋሞ ጎፋ ብርብር ማርያም፤ጎጃም መርጡለማርያምና ዲማ ጊዮርጊስ፤ የብሐ ጊዮርጊስ ከፋ፤የዋሻ ሚካኤል ሰላሌ፤ የጀንባ ሚካኤል ሰማዳ፤ እንዲሁም በአዲስ አበባ የካ ሚካኤልንና የረር በዓታ ተጠቃሽ ናቸው። ከሁሉም በላይ ዓለም ዛሬም ድረስ የሚገረምባቸውን የአክሱም ሀውልቶች ያቆሙ ናቸው፤ 33 ሜትር ተኩል ድንጋይን ከየት አመጡት እንዴትስ ቀረጹት እንዴትስ ብለው አቆሙት ይህ የእግዚያብሔር ተአምር ነው እንጂ፤ እኛስ እጹብ ግሩም ብቻ ብለን እናልፋለን። በኢትዮ ከነገሱ ከጥንት ነገስታት እንደ አብርሃና አጽብሃ በርካታ ታሪክን አኑሮልን ያለፈ ንጉስ የለም ብንል አልተሳሳትንም፤ እነዚህ ቅዱሳን የኢትዮጵያን ድንበር አስፍተው ክርስትናን አጽንተው ያስረከቡን ዋኖቻችን ናቸው፤ሁለቱም በተለያየ ዓመተ ምህረት ጥር 4 ቀን አርፈዋል፤ኢትዮጰያ ውስጥ በስማቸው ሰባት ቤተክርስቲያን እንዳላቸው ሊቀ ብርሃናት መርቆሪዎስ አረጋ የቅዱሳን ታሪክ በሚለው መጽሀፋቸው ጠቅሰውታል፤ ጥር 4 ቀን በተለይ በሰሜኑ ኢትዮጵያ በደማቁ ተከብረው ይውላሉ። በረከታቸው ይደርብን።