በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
ጥቅምት 22 ... ዕረፍቱ ለቅዱስ ሉቃስ ወንጌላዊ
በዚህች ቀን ወንጌላዊው ቅዱስ ሉቃስ ዐረፈ:: የሉቃስ ወንጌልንና የሐዋርያት ሥራን የጻፈልን አባት ነው::
ቁጥሩ ከ 72ቱ አርድዕት ነው፤ቀድሞ ዶክተር ነበር መድሐኒት ቀምሞ የሥጋ በሽታን የሚፈውስ በኋላ ግን
ወንጌልን ሰብኮ የነፍስን ቁስልን የሚፈውስ ሆኗል::
ወንጌሉን መቼ ጻፈው? ቢሉ ጌታ ባረገ በ 22 ዓመቱ የት ጻፈው?መቄዶኒያ በምን ቋንቋ? በዮናኒ፤ማቴዎስ
በዕብራይስጥ፤ ማርቆስ በሮማይስጥ፤ ዮሐንስ በጽርዕ ቋንቋ ነው የጻፉት። ቅዱስ ሉቃስ መጀመሪያ ዮሐንስን
ተከትሎ ወንጌል ሰበከ በኋላም ከቅዱስ ጳውሎስ ጋር ሮም ሲሰብኩ ቅዱስ ጳውሎስ በኔሮን እጅ በሰማዕትነት
ዐረፈ፤ ብቻውን እየተዘዋወረ ወንጌለ መንግሥተ ሰማያትን ሰበከ::
የክርስቲያኖች ቁጥር በዛ አብያተ ጣኦታትንም አፈራረሰ በዚህም ንጉሱ ተቆጣ ሸንጎ ፊት አቅርቦም፤ ወንጌልን
የጻፈች እጅህ ይህች ነችን? ብሎ ቀኝ እጁን ቆረጠው፤ ቅዱስ ሉቃስም "ኢየሱስ ክርስቶስ የተቆረጠ እጅ
አይደለም የተቆረጠች ነፍስንም ይቀጥላል::" ብሎ በግራ እጁ የተቆረጠች እጁን አንስቶ እንደ ቀድሞ አደረጋት፤
በወንጌል ላይ ጌታችን የተቆረጠች የማልኮስን ጆሮ ወደ ቀደመ ቦታዋ እንደ መለሳት ልብ ይሏል፤ "በእኔ የሚያምን
እኔ የማደርገውን ያደርጋል ከኔም በላይ ያደርጋል::" ያለ ጌታ የታመነ ነው። ቅዱስ ሉቃስ ያደረገውን ተአምር
ተመልክተው 267 ወታደሮችና መኮንኑ በክርስቶስ አምነዋል፤ ንጉሱም በሰይፍ አስፈጅቷቸዋል፤ ቅዱስ ሉቃስንም
ጥቅምት 22 ቀን አንገቱን ቆርጦ በአሸዋ ከተሞላ ስልቻ ጋር አድርገው ወደ ባሕር ጥለውታል::
"... ምስለ ኤጲስቆጶስ ያዕቆብ ዘኢየሩሳሌም
ይምጽኡ ኀቤነ ለባርኮትነ ዮም
ማርቆስ ዘኣንበሳ ወሉቃስ ዘላሕም።"
ከሐዋርያው በረከት ያሳትፈን፤ አሜን! አሜን! አሜን!
No comments:
Post a Comment