Wednesday, 27 November 2013

ወበዛቲ ዕለት

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡

ኅዳር ፲፰ ዕረፍቱ ለሐዋርያ ፊልጶስ አሐዱ እም ፲፪ቱ ሐዋርያት (ከ፲፪ቱ ሐዋርያት አንዱ የሆነው ሐዋርያው ፊሊጶስ አረፈ)
“ክቡር ሞቱ ለጻድቅ በቅመ እግዚአብሔር” (የቅዱሳኑ ሞት በእግዚአብሔር ፊት የከበረ ነው።) መዝ.፻፲፭፡፲፭ (115፡15)

ፊሊጶስ ማለት ሥውር ቦታ ማለት ነው።

ሁለት ፊልጶስ አሉ :: አንዱ ጥቅምት 14 ቀን መታሰቢያውን የምናከብርለት ኢትዮጰያዊውን ጀንደረባ ያጠመቀውን ዲያቆኑ ፊሊጶስ ነው። 
ሀገረ ስብከቱ አፍቅራያ ነው። ሁለተኛው ይህ ዛሬ በዓሉን የምናከብርለት ቁጥሩ ከ፲፪ ሐዋርያት የሆነ ፊልጶስ ነው:: በተጨማሪም ሐዋርያው
ቅዱስ ናትናኤልን የጠራው ነው::

ቅዱስ ፊልጶስ አሐዱ እም ፲፪ቱ ሐዋርያት

“በነገው ኢየሱስ ወደ ገሊላ ሊወጣ ወደደ፥ ፊልጶስንም አገኘና። ተከተለኝ አለው።” ፊልጶስም ከእንድርያስና ከጴጥሮስ ከተማ ከቤተ ሳይዳ ነበረ።
(ዮሐ.፩፡፵፬) ይላል። ሐዋርያት ዓለምን ዞረው ለማስተማር ዕጣ ሲያወጡ ለፊሊጶስ ከወርቅ የተሰራ ኦሞራ የሚያመልኩ ሰዎች ያሉበት አገር 
ደረሰው ገድለ ሐዋርያት ላይ አፍራቅያ ይለዋል። የአገሩን ስም ቱርክ አካባቢ የሚገኝ ነው፤ ወደ ከተማው ገብቶ ወንጌለ መንግስተ ሰማያትን ሰበከ።
ትልቅ አምድ አግኝተው ወጥተህ መስክር ብለው አምዱን አውርደው አወጡት። ፤ዓምዱ ከቦታው ተመለሰ። ከዚያ ላይ ሆኖ ሲመሰክር ንውጽውጽታ
ሆነ። በድንጋጼም የሞቱ አሉ። የቀሩት “አመነ በአምላክክሙ ይእዜሰ አድኀኑነ ከመ ኢንሙት” /በአምላካችን አምነናል እንዳንሞት አድኑን አሏቸው።
ብዙዎችንም አሳመነ አጠመቃቸው፤ አቆረባቸውም፤ ቤተክርስቲያን ሰራላቸው፤ ካህንና ዲያቆንም ሾመላቸው። ከዚህ በኋላ ሕዝቡን ከአልኮተ ጣኦጠ
ወደ ገቢረ ጽድቅ ወደ አምልኮተ እግዚአብሔር መልሶ ሲኖር ጥቅማቸው የጎደለባቸው ነቢያተ ሐሰት ካህናተ ጣኦት ከንጉሱ ጋር ነገር ሰርተው አጣሉት፤
አስረው ደበደቡት፤ ቁልቁል ሰቅለውም ገደሉት። ይህም የሆነው በዛሬዋ ቀን ማለትም ኀዳር ፲፰ ቀን ነው። ሥጋውን እናቃጥላለን ብለው ወዲያ ወዲህ
ሲሉ መልአኩ ከመካከላቸው ነጥቆ ኢየሩሳሌም አድርሶታል። ኋላ ግን ከክፋታቸው ተመልሰው ሲማጸኑ መልሶላቸው በሥርዓት ቀብረውታል።

“ተዘከሩ መኳንንቲክሙ ዘነገሩክሙ ቃለ እግዚአብሔር” /የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሩአችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ፥ የኑሮአቸውንም ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነታቸው ምሰሉአቸው። ዕብ.፲፫፡፯ (ዕብ.13፡7)

ስብሐት ለእግዚአብሔር ኪያነ ዘፈጠረ ከመ ናምልኮ
ስብሐት ለማርያም እመ አምላክ እግዝእትነ ወመድኃኒትነ
ስብሐት ለመስቀለ ክርስቶስ ዕፀ መድኃኒት ኃይልነ ወፀወንነ


የሐዋርያው በረከት በሁላችን ላይ ይደርብን አሜን። 



No comments:

Post a Comment