Tuesday 29 August 2017

የማይቀርበት ጉባኤ ነውና የቤተክርስቲያን ዶግማ ትምህርቶች ከሆኑት አንዱ ስለ ነገረ ቅዱሳን በሰፊው የሚሰጥበት መጽሐፍ ቅዱስን መሠረት በማድረግ ስለ ቅዱሳን ክብር ፣አማላጅነት ስለዚህ ሁላችሁም ተጋብዛችኋል ዕለቱም ሁለት ታላላቅ ጉባኤያትን የምናከናውንበት ቀኑ ገጥሟልና ሳምንታዊው ልዩ ጉባኤያችንን እንዲሁም በዕለቱ ብዙ ቅዱሳን የሚታሰቡበት በደብራችን የቅድስት ክርስቶስ ሠምራን በዐል የምናከብርበት ዕለት ስለሆነ በዕለቱም ለምሳሌ የጻድቁ አባታችን የአቡነ ተክለሃይማኖት እና ታላቁ ሰማዕት እና ሐዋርያ የሆነው ቅዱስ ቶማስ ዘመርአስ ይታሰባሉና ሁሉን ተምረን በዕለቱ ባያልቅም በጥቂቱም ቢሆን ነገረ ቅዱሳንን እንማራለንና የቅዱሳኑን በረከት፣ምልጃ እንድናገኝ ላልሰሙትም አሰምተን ሁላችንም በዕለቱ ተገኝተን የበረከቱ ተካፋዮች እንድንሆን የቀ/ደ/ሰ/ መድሐኔዓለም ስብከተ ወንጌል ጥሪውን ያስተላልፋል መጽሐፍ እንደሚል የሰማም ና ይበል ነውና የሚለው በታላቁ እና ታሪካዊው ደብራችን የክርስቶስ ሠምራ ንግሥ መኖሩን ሁሉ ልናሰማ ይገባናልና እንደ እምነታችሁ መጠን እግዚአብሔርን አመስግኑት ነውና የተባልነው እንደየጸጋችን የቻልን በማኅሌቱም፣በኪዳኑም፣በንግሡም፣በቅዳሴውም ፣በጉባኤውም እንድንገኝ ሥራ ፣ትምህርት የተለያየ ጉዳይ ያለብን ሰዓታችንን አመቻችተን በተወሰነው ተገኝተን የእግዚአብሔር ምሕረት የቅዱሳንን በረከት እንድንሳተፍ ቤተክርስቲያን በድጋሚ ጥሪዋን ታስተላልፋለች!!!
አምላከ ጊዮርጊስ ሃገራችንን ኢትዮጵያን ሰላም ያድርግልን ሀይማኖታችንን ይጠብቅልን"

No comments:

Post a Comment