Wednesday 27 November 2013

ወበዛቲ ዕለት

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡

ኅዳር ፲፰ ዕረፍቱ ለሐዋርያ ፊልጶስ አሐዱ እም ፲፪ቱ ሐዋርያት (ከ፲፪ቱ ሐዋርያት አንዱ የሆነው ሐዋርያው ፊሊጶስ አረፈ)
“ክቡር ሞቱ ለጻድቅ በቅመ እግዚአብሔር” (የቅዱሳኑ ሞት በእግዚአብሔር ፊት የከበረ ነው።) መዝ.፻፲፭፡፲፭ (115፡15)

ፊሊጶስ ማለት ሥውር ቦታ ማለት ነው።

ሁለት ፊልጶስ አሉ :: አንዱ ጥቅምት 14 ቀን መታሰቢያውን የምናከብርለት ኢትዮጰያዊውን ጀንደረባ ያጠመቀውን ዲያቆኑ ፊሊጶስ ነው። 
ሀገረ ስብከቱ አፍቅራያ ነው። ሁለተኛው ይህ ዛሬ በዓሉን የምናከብርለት ቁጥሩ ከ፲፪ ሐዋርያት የሆነ ፊልጶስ ነው:: በተጨማሪም ሐዋርያው
ቅዱስ ናትናኤልን የጠራው ነው::

ቅዱስ ፊልጶስ አሐዱ እም ፲፪ቱ ሐዋርያት

“በነገው ኢየሱስ ወደ ገሊላ ሊወጣ ወደደ፥ ፊልጶስንም አገኘና። ተከተለኝ አለው።” ፊልጶስም ከእንድርያስና ከጴጥሮስ ከተማ ከቤተ ሳይዳ ነበረ።
(ዮሐ.፩፡፵፬) ይላል። ሐዋርያት ዓለምን ዞረው ለማስተማር ዕጣ ሲያወጡ ለፊሊጶስ ከወርቅ የተሰራ ኦሞራ የሚያመልኩ ሰዎች ያሉበት አገር 
ደረሰው ገድለ ሐዋርያት ላይ አፍራቅያ ይለዋል። የአገሩን ስም ቱርክ አካባቢ የሚገኝ ነው፤ ወደ ከተማው ገብቶ ወንጌለ መንግስተ ሰማያትን ሰበከ።
ትልቅ አምድ አግኝተው ወጥተህ መስክር ብለው አምዱን አውርደው አወጡት። ፤ዓምዱ ከቦታው ተመለሰ። ከዚያ ላይ ሆኖ ሲመሰክር ንውጽውጽታ
ሆነ። በድንጋጼም የሞቱ አሉ። የቀሩት “አመነ በአምላክክሙ ይእዜሰ አድኀኑነ ከመ ኢንሙት” /በአምላካችን አምነናል እንዳንሞት አድኑን አሏቸው።
ብዙዎችንም አሳመነ አጠመቃቸው፤ አቆረባቸውም፤ ቤተክርስቲያን ሰራላቸው፤ ካህንና ዲያቆንም ሾመላቸው። ከዚህ በኋላ ሕዝቡን ከአልኮተ ጣኦጠ
ወደ ገቢረ ጽድቅ ወደ አምልኮተ እግዚአብሔር መልሶ ሲኖር ጥቅማቸው የጎደለባቸው ነቢያተ ሐሰት ካህናተ ጣኦት ከንጉሱ ጋር ነገር ሰርተው አጣሉት፤
አስረው ደበደቡት፤ ቁልቁል ሰቅለውም ገደሉት። ይህም የሆነው በዛሬዋ ቀን ማለትም ኀዳር ፲፰ ቀን ነው። ሥጋውን እናቃጥላለን ብለው ወዲያ ወዲህ
ሲሉ መልአኩ ከመካከላቸው ነጥቆ ኢየሩሳሌም አድርሶታል። ኋላ ግን ከክፋታቸው ተመልሰው ሲማጸኑ መልሶላቸው በሥርዓት ቀብረውታል።

“ተዘከሩ መኳንንቲክሙ ዘነገሩክሙ ቃለ እግዚአብሔር” /የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሩአችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ፥ የኑሮአቸውንም ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነታቸው ምሰሉአቸው። ዕብ.፲፫፡፯ (ዕብ.13፡7)

ስብሐት ለእግዚአብሔር ኪያነ ዘፈጠረ ከመ ናምልኮ
ስብሐት ለማርያም እመ አምላክ እግዝእትነ ወመድኃኒትነ
ስብሐት ለመስቀለ ክርስቶስ ዕፀ መድኃኒት ኃይልነ ወፀወንነ


የሐዋርያው በረከት በሁላችን ላይ ይደርብን አሜን። 



Sunday 3 November 2013

ወበዛቲ ዕለት

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

እንኳን ለጻድቁ ኣባታችን ኣቡነ ተክለሃይማኖት
         ለእናታችን ቅድስት ክርስቶስ ሰምራና 
          ለሰማዕቱ ህጻን ኣባኖብ 
                                 ወርሃዊ መታሰብያ በሰላም ኣደረሰን።

ጸሎታቸውና በረከታቸው ከሁላችንም ጋር ይሁን ኣሜን።







Thursday 31 October 2013

Ethiopian Orthodox Mezmur-Be Werke Kelem Tesifeshal - Zemarit Tsigereda


Ethiopian Orthodox Tewahedo Mezmur - Kidist Arsema - Zemarit Tsegereda Tilahun


Zemari Yilma Hailu - Zim atbelu



Zemari Yilma Hailu - Besew zend bimuatet tesfana desta...


Ethiopian Orthodox Mezmur - Yeab kal Akbrosh - Yilma Hailu - የአብ ቃል አክብሮሽ

New Ethiopian orthodox mezmur Yilma Hailu Selam Le ki

ወበዛቲ ዕለት

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

ጥቅምት 22 ... ዕረፍቱ ለቅዱስ ሉቃስ ወንጌላዊ 

በዚህች ቀን ወንጌላዊው ቅዱስ ሉቃስ ዐረፈ:: የሉቃስ ወንጌልንና የሐዋርያት ሥራን የጻፈልን አባት ነው:: 
ቁጥሩ ከ 72ቱ አርድዕት ነው፤ቀድሞ ዶክተር ነበር መድሐኒት ቀምሞ የሥጋ በሽታን የሚፈውስ በኋላ ግን
ወንጌልን ሰብኮ የነፍስን ቁስልን የሚፈውስ ሆኗል::

ወንጌሉን መቼ ጻፈው? ቢሉ ጌታ ባረገ በ 22 ዓመቱ የት ጻፈው?መቄዶኒያ በምን ቋንቋ? በዮናኒ፤ማቴዎስ

በዕብራይስጥ፤ ማርቆስ በሮማይስጥ፤ ዮሐንስ በጽርዕ ቋንቋ ነው የጻፉት። ቅዱስ ሉቃስ መጀመሪያ ዮሐንስን
ተከትሎ ወንጌል ሰበከ በኋላም ከቅዱስ ጳውሎስ ጋር ሮም ሲሰብኩ ቅዱስ ጳውሎስ በኔሮን እጅ በሰማዕትነት
ዐረፈ፤ ብቻውን እየተዘዋወረ ወንጌለ መንግሥተ ሰማያትን ሰበከ::

የክርስቲያኖች ቁጥር በዛ አብያተ ጣኦታትንም አፈራረሰ በዚህም ንጉሱ ተቆጣ ሸንጎ ፊት አቅርቦም፤ ወንጌልን

የጻፈች እጅህ ይህች ነችን? ብሎ ቀኝ እጁን ቆረጠው፤ ቅዱስ ሉቃስም "ኢየሱስ ክርስቶስ የተቆረጠ እጅ
አይደለም የተቆረጠች ነፍስንም ይቀጥላል::" ብሎ በግራ እጁ የተቆረጠች እጁን አንስቶ እንደ ቀድሞ አደረጋት፤
በወንጌል ላይ ጌታችን የተቆረጠች የማልኮስን ጆሮ ወደ ቀደመ ቦታዋ እንደ መለሳት ልብ ይሏል፤ "በእኔ የሚያምን
እኔ የማደርገውን ያደርጋል ከኔም በላይ ያደርጋል::" ያለ ጌታ የታመነ ነው። ቅዱስ ሉቃስ ያደረገውን ተአምር
ተመልክተው 267 ወታደሮችና መኮንኑ በክርስቶስ አምነዋል፤ ንጉሱም በሰይፍ አስፈጅቷቸዋል፤ ቅዱስ ሉቃስንም
ጥቅምት 22 ቀን አንገቱን ቆርጦ በአሸዋ ከተሞላ ስልቻ ጋር አድርገው ወደ ባሕር ጥለውታል::

"... ምስለ ኤጲስቆጶስ ያዕቆብ ዘኢየሩሳሌም
ይምጽኡ ኀቤነ ለባርኮትነ ዮም
ማርቆስ ዘኣንበሳ ወሉቃስ ዘላሕም።"

ከሐዋርያው በረከት ያሳትፈን፤  አሜን! አሜን! 
አሜን!

Tuesday 29 October 2013

ወበዛቲ ዕለት

ጥቅምት 20 በዚህች ቀን አባ ዮሐንስ ሐጺር አረፈ፤ ቁመቱ አጭር ስለሆነ ነው ዮሐንስ ሐጺር የተባለው፤
በ18 ዓመቱ በገዳመ አስቄጥስ መንኩሶ በተጋድሎ ኖረ፤ ይህ አባት ነጽሮተ ስሉስ ቅዱስ የደረሰ አባት ነው፤
እዚህ ደረጃ የደረሱ አባቶች ቀና ቢሉ ሥላሴን ይመለከታሉ ዝቅ ቢሉ እንጦሮጦስን ያያሉ፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን 
የገዳሙ አብምኔት ሊፈትነው ብሎ ደረቅ እንጨት ሰጠው ይህንን ተክለህ አለምልመህ ፍሬውን አምጣልኝ አለው፤
እርሱም እንጨቱን ተከለው 3 ዓመት ሙሉ ከሩቅ ቦታ ውሃ እየቀዳ አጠጣው በ3ኛው ዓመት ጸደቀ ለመለመ ትልቅ 
ዛፍም ሆነ፤ ፍሬም አፈራ፤ መነኮሳቱ ይህ የትእግስት ውጤት ነው ብለው ፍሬውን ቀምሰውለታል፡፡ አንዲት አትናስያ 
የምትባል ሴት ነበረች፤ መጀመሪያ ጻድቅ ነበረች በኋላ ላይ በዝሙት ወደቀች ዘማዊም ሆነች፤ የቀድሞ ቅድስናዋን 
የሚያውቁ መነኮሳት ሊመክሯት ቢመጡ ሳቀችባቸው አሁን ማንን እንላክ ብለው አሰቡ ዮሐንስ ሐጺርን ላኩት፤ 
ተራ ሰው መስሎ ገባ፤ ለዝሙት የመጣ መስሏት ተቀበለችው፤ተጫወት አለችው ዮሐንስ ሐጺር ማልቀስ ጀመረ 
ምን ያስለቅስሃል ትለዋለች መልክሽ ደስ ብሎኝ ይላታል፤ደስ የሚል መልክ ያስቃል እንጂ መች ያስለቅሳል ትለዋለች 
የለም ነገ ገሃነም እንደምትወርጂ ታይቶኝ ነው አንድም ብዙ አጋንንት በሰውነትሽ ሲወጡ ሲወርዱ አያለሁ አላት፤ 
ደነገጠች ምን ይሻለኛል ትለዋለች፤ ንስሃ ገቢ ማን ያስታርቀኛል ኃጢአቴ ብዙ ነው ትለዋለች፤እኔ አስታርቅሻለሁ 
ተከተይኝ ብሎ ወጣ ልዋል ልደር ሳትል በሯን እንደተከፈተ ተከተለችው በልስላሴ የኖረ እግር ተበጣጥሶ በበዙ ደካም 
ሲመሽ ከገዳሙ ደረሱ፤የምታርፍበትን ቦታ ለይቶ ሰጣት፤ ሌሊት ለጸሎት ሲነሳ መላእክት ሲወጡ ሲወርዱ ያያል፤ 
ምንድን ነው ብሎ አንዱን መልአክ ይጠይቀዋል፤ትላንትና አንተን ተከትላ የመጣችው ሴት አርፋ ነፍሷን እያሳረግን
ነው ይለዋል፤ እግዚኦ ንስሃ ሳትገባ ብሎ ይደነግጣል፤ አንተን ልትከተል ገና አንድ እግሯን ከቤት ስታወጣ ኃጢያቷ
በሙሉ ተፍቆላታል፤ አሁን ወደ ገነት እየወሰድናት ነው ይለዋል፤ዮሐንስ ተገረመ፤የመቃብሯስ ነገር አለው፤ 
አንበሶች ይመጣሉ ቦታውን ለካላቸው ይለዋል፤አንበሶች ቆፍረውለት ቀብሯታል፤ ዮሐንስ ሐጺር በተጋድሎ ኖሮ
ጥቅምት 20 ዕለት አርፏል፤ በረከቱ ይደርብን፡፡


Monday 14 October 2013

ወበዛቲ እለት

ጥቅምት 4 
በዚህች ቀን የኢትዮጵያ ባለውለታዎች፤ ኢትዮጵያን ኢትዮጵያ እንድትሆን ትልቁን ድርሻ ያበረከቱ አብርሃና አፅብሃ የእረፍት ቀናቸው ነው፤እነዚህ ሁለት ጻድቅ ነገስታት ወንድማማች ሲሆኑ የክርስትና እምነትን በኢትዮጽያ ያበሩ አማናዊ ጥምቀትንና ቁርባን ያስጀመሩ ከመሆናቸው ባሻገር ከ 154 በላይ አብያተክርቲያናት አንጸዋል፤ ከነዚህም በተለይ ዋንኞቹ ትግራይ ውስጥ ገልአርታ ቀመር አርብአቱ እንስሳ፤ጋሞ ጎፋ ብርብር ማርያም፤ጎጃም መርጡለማርያምና ዲማ ጊዮርጊስ፤ የብሐ ጊዮርጊስ ከፋ፤የዋሻ ሚካኤል ሰላሌ፤ የጀንባ ሚካኤል ሰማዳ፤ እንዲሁም በአዲስ አበባ የካ ሚካኤልንና የረር በዓታ ተጠቃሽ ናቸው። ከሁሉም በላይ ዓለም ዛሬም ድረስ የሚገረምባቸውን የአክሱም ሀውልቶች ያቆሙ ናቸው፤ 33 ሜትር ተኩል ድንጋይን ከየት አመጡት እንዴትስ ቀረጹት እንዴትስ ብለው አቆሙት ይህ የእግዚያብሔር ተአምር ነው እንጂ፤ እኛስ እጹብ ግሩም ብቻ ብለን እናልፋለን። በኢትዮ ከነገሱ ከጥንት ነገስታት እንደ አብርሃና አጽብሃ በርካታ ታሪክን አኑሮልን ያለፈ ንጉስ የለም ብንል አልተሳሳትንም፤ እነዚህ ቅዱሳን የኢትዮጵያን ድንበር አስፍተው ክርስትናን አጽንተው ያስረከቡን ዋኖቻችን ናቸው፤ሁለቱም በተለያየ ዓመተ ምህረት ጥር 4 ቀን አርፈዋል፤ኢትዮጰያ ውስጥ በስማቸው ሰባት ቤተክርስቲያን እንዳላቸው ሊቀ ብርሃናት መርቆሪዎስ አረጋ የቅዱሳን ታሪክ በሚለው መጽሀፋቸው ጠቅሰውታል፤ ጥር 4 ቀን በተለይ በሰሜኑ ኢትዮጵያ በደማቁ ተከብረው ይውላሉ። በረከታቸው ይደርብን።

Monday 30 September 2013

ግሸን ደብረከርቤ ዳግማዊት ጎልጎታ

እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ክብረ በዓል በሰላም አደረሰን !

ግሸን ከደሴ ከተማ 82ኪ.ሜ ርቀት ላይ በወሎ ክ/ሐገር በአንባሰል ወረዳ ውስጥ በሃይቅ እና በመቅደላ በደላንታና በየጁ መካከል በበሽሎ ወንዝ አዋሳኝ ከፍተኛ በሆነ ተራራ ላይ የምትገኝ ገዳም ናት::
የበሸሎን ወንዝ ተሻግረን ሰማይ ጥግ የደረሱ የሚመስሉትን ተራሮች ወጥተን በስተመጨረሻ መግቢያ አንድ በር የሆነ እና ከተራራው አናት ላይ በሚገኝ ስፋራ ላይ በ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስም የታነጸ እና ግማደ መስቀሉ የሚገኝበት የ እግዚአብሔር አብ አብያተ ክርስቲያናት ይገኛሉ::
በ1942 ዓ.ም አቡነ ሚካኤል ጳጳስ ዘጎንደር ከዚህም ጋር ''መንፈሳዊ መናኝ'' በመባል የሚታወቁት ደገኛ አባት ያሰሩት ቅዱስ ቤተ ክርስቲያንም ይገኛል::

ግሸን ይህን የአሁኑን መጠሪያ ስም ከማግኘትዋ በፊት በተለያየ መጠሪያ ስሞች ትታወቅ ነበር::
በመጀመሪያ በአጼ ድልነአድ ዘመነ መንግስት በ896ዓ.ም ሃይቅ ደብረ እስጢፋኖስ ሲመሰረት ''ሐይቅ ደብረ ነጎድጉዋድ'' ተብሎ ሲሰየም ግሸንም በሃይቅ ግዛት ውስጥ ስለሆነች ስምዋ ''ደበረ-ነጎጉዋድ'' ተባለች::
ይህን መጠሪያ ስምዋን እንደያዘች እስከ አስራአንደኛው ክ/ዘመን ድረስ ቆየች:: በ11ኛው ክ/ዘ ላይ በኢትዮጵያ ነግሶ የነበረው ጻድቁ ንጉስ ላሊበላ ከቁዋጥኝ ድንጋይ ፈልፍሎ የሰራው ቤተ መቅደስ በእግዚአብሔር አብ ስም ይጠራ ስለነበር ግሸንም ''ደብረ እግዚአብሔር'' ተብላ መጠራት ጀመረች:: ነገር ግን በዚህ ስም በመጠራት ብዙም ሳይቆይ ስምዋ ተለውጦ '' ደብረ ነገሥት'' ተባለች:: ደብረ ነገስት የተባለችውም ነገስታቱ ይማጸኑባት የክብርና የማእረግ እቃዎች ያስቀምጡባታል; የነገስታቱ የመሳፍንቱ ልጆችም የቤተ መንግስት አስተዳደር የሚማሩበት ስፍራ ስለነበረች ነው::
እንደገና ደግሞ በ1446ዓ.ም ኢትዪጵያዊው ፈላስፋ እየተባሉ በሚጠሩት በአጼ ዘርዓ ያዕቆብ ዘመነ መንግስት ግማደ መስቀሉ መጥቶ በዚህ ቅዱስ ስፍራ ሊያርፍ ደብረ- ነግሥት መባልዋ ቀርቶ ''ደብረ- ከርቤ'' ተባለች:: የደብርዋ አስተዳዳሪዋ የማዕረግ ስም ስም ''መምህር እስራኤል ዘደብረ ከርቤ'' ይባል ነበር::
ዓጼ ዘርያቆብ ግማደ መስቀሉን አሸክመው እየገሰገሱ ከብዙ ድካምና ፍለጋ በሁዋላ ወደ ተራራዋ
በመምጣታቸው ''ገሰገሱ'' ከሚለው ቃል በግዕዝ
''ጌሠ'' የሚል ትርጉዋሜ ያለው በመሆኑ ከ''ጌሠ'' በጊዘ ብዛት ግሸን የሚል ቃል በመፍጠሩ ''ግሸን'' የሚለው ስያሜ ሊሰጣት ችሉአል::
ግሸን ማርያም የስም ስያሜዋ ይህን ይምሰል እንጂ የቦታው መገኘት የቆየ ታሪክ አለው::
ዓጼ ዘርዓ-ያዕቆብ ግማደ መስቀሉን ይዘው ከመምጣታቸው ከ932 አመታት በፊት ; ቅዱስ ላሊበላም ደበረ- እግዚአብሔርን ከመመስረቱ ከ583 አመት በፊት ; እነ አባ ኢየሱስ ሞዓ ሃይቅ ደብረ ነጎድጉዋድን ከመመስረታቸው 349 አመት አስቀድሞ በአንድ ደገኛ አባት ተመሰረተች::
ለዓጼ ካሌብ እንደ ነፍስ አባት/የንስሃ አባት ሁነው የሚያገለግሉት አባ ፍቃደ ክርስቶስ የሚባሉት መንፈሳዊ መናኝ በየመን በሃገረ ናግራን ላይ ይኖሩ ስለነበር በናግራን ተራራ ላይ የሚገኙ ሁለት ጽላቶችን ኢትዮጵያን ወስደው እንዲያኖሩ ከፈጣሪያቸው በጸሎት እንደተገለጸላቸው ለንሥሃ ልጃቸው ለዓጼ ካሌብ በመናገራቸው ንጉሱም ፈቅደው አባ ፍቃደ ክርስቶሥም ሁለቱን ጽላቶች አሸክመው ሸሎ ወንዝን ተሻግረው አቀበቱን ወጥተው ወደ መስቀለኛው አምባ ጥግ ሲደርሱ ወደ አምባው ጫፍ ለመውጣት ሰርጥ ሲፈልጉ የአምባውን ዙሪያ በገደሉ ላይ ንብ ሰፍሮ የማሩ ሰፈፍ ጨረቃ መስሎ በማየታቸው የአካባቢውን እና የእግዚአብሔርን ተፈጥሮ ስጦታ ሲያደንቁ ይህስ ''አምባ ''አሰል'' ነው በማለት ተናገሩ:: ''አሰል'' የሚለው ቃል በአረብኛ ''ማር'' ሲሆን ሙሉ ትርጉሙ ''የማር አምባ'' ማለት ነው:: ከዚያን ጊዘ ጀምሮ እስከአለንበት ዘመን ድረስ የግሸን ማርያም አካባቢ ወረዳ ''አምባሰል'' ተብሎ ይጠራል::
አባ ፈቃደ ክርስቶሥ በ517ዓ.ም በተራራው ላይ ወጥተው መጠነኛ ጎጆ በመቀለስ ሁለቱን ጽላቶች አስቀመጡ:: ሁለቱ ጽላቶችም ''ታቦተ ቅድስት ድንግል ማርያም እና ታቦተ እግዚአብሔር አብ'' ናቸው::
ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን!

Tuesday 24 September 2013


Yehulachin abat Abune Gorgoriwos

ነገረ መስቀል


እንኳን ለጌታችንና ለመድሐኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ 
የመስቀል ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!!

ነገረ ቅዱሣን ወቅዱሣት

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡ 
ሰላም ለእናንተ ይሁን የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የአስራት ልጆች የቅዱሣን ወዳጆች!
እንኳን ለጻድቁ አባታችን አቡነ አረጋዊ እና ለጻድቁ አባታችን አቡነ ገብረ ክርስቶስ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን!

የጻድቁ አባታችን አቡነ አረጋዊ እና የጻድቁ አባታችን አቡነ ገብረ ክርስቶስ ረዲዔታቸው በረከታቸው ምልጃና ጸሎታቸው 
ከኛ ጋር ለዘላለም ጸንቶ ይኑር አሜን!!!





ነገረ ቅዱሣን ወቅዱሣት


 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡ 
ሰላም ለእናንተ ይሁን የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የአስራት ልጆች የቅዱሣን ወዳጆች!
እንኳን ለጻድቁ አባታችን አቡነ ገብረ ክርስቶስ እና ለጻድቁ አባታችን አቡነ አረጋዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን፡፡

የጻድቁ አባታችን አቡነ ገብረ ክርስቶስ እና የጻድቁ አባታችን አቡነ አረጋዊ ረዲዔታቸው በረከታቸው ምልጃና ጸሎታቸው 
ከኛ ጋር ለዘላለም ጸንቶ ይኑር አሜን!!!

ነገረ መስቀል

መስቀል ኃይልነ መስቀል ቤዛነ መስቀል ጽንዕነ መስቀል መድሐኒተ ነፍስነ...

ነገረ ቅዱሣን ወቅዱሣት


 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡ 

ሰላም ለእናንተ ይሁን የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የአስራት ልጆች የቅዱሣን ወዳጆች?

እንኳን ለጻድቁ አባታችን አቡነ አረጋዊ እና ለጻድቁ አባታችን አቡነ ገብረ ክርስቶስ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን፡፡
የጻድቁ አባታችን አቡነ አረጋዊ እና የጻድቁ አባታችን አቡነ ገብረ ክርስቶስ ረዲዔታቸው በረከታቸው ምልጃና ጸሎታቸው 
ከኛ ጋር ለዘላለም ጸንቶ ይኑር አሜን!!!

Sunday 22 September 2013

ነገረ ማርያም


ጊሸን ደብረ ከርቤ

ውል ውል አለኝ ደጅሽ...

የገሐነም ደጆች አይችሏትም

አክሱም ጽዮን ማርያም
የእመቤታችን ልመናዋ ክብሯ የልጇም ቸርነት በመላው ሕዝበ ክርስቲያን ላይ ይደር አሜን!!!

የገሐነም ደጆች አይችሏትም

የእግዚአብሔርን ታምር ተመልከቱ ቦታው ሶርያ ነው የቤተክርስትያኑ ስም Saydania ይባላል::
እንደተለመደው የዘወትር ፀሎቷ ለህዝቧም ለዓለምም እያደረሰች ባለችበት ሰዓት አንድ ሰው ወደ 
መነኩሴዋ እማሁይ Marina Almaloof ቀርቦ 
"ሥዕለት ለመስጠት ነበር፤ እባከዎ ይሄን ብር ሳጥን ውስጥ ያስገቡልኝ፤ በእጅ የያዘውን 160ሳ.ሜ
የሆነውን ሻማ ይሄን ደግሞ በስዕለ ማርያም ፊት ያብሩልኝ፤ እኔ በጣም ሰለምቸኩል ነው" ይልና 
በፍጥነት ይወጣል:: መነኩሴዋም ክብሪት አነሱ አቤቱ የሰራዊት ጌታ ስዕለቱን ተቀበለው አሉ፡፡
ክብሪቱን ጫሩ ሻማው ጫፍ አቀረቡት ሻማው ሳይቃጠል ክብሪቱ ተቃጥሎ አለቀ በድጋሜ ሞከሩ፤
ሞከሩ፡፡ ሻማው ባለመቃጠሉ እየተገረሙ ከወደ ውጪ ጩኸት ተሰማ፡፡ መነኩሴዋም ወጡ ከታች
መጨረሻ ደረጃው ላይ አንድ ሰው ወድቆ የሞተ ሰው ያያሉ፡፡ "ይሄ አሁን ስለት የሰጠኝ ሰውየ ነው"
አሉ፡፡ ስልክ ለሶርያ ፖሊስ ተደወለ፤ በፍጥነት መጡ ነገሩ ተጣራ፡፡ እስኪ ሻማው? አለ ፖሊስ፡፡ 
ሻማው ተመረመረ በውስጡ ዳይናሜት TNT የተባለ አደገኛ ተቀጣጣይ ፈንጆች የተሞላ ሆኖ ተገኘ
ሰውየውን የሚያውቅ ሠው አልተገኝም፡፡ ሰውየው በልብ ድካም ነው የሞተው ተባለ፡፡ ወላዲተ አምላክ
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ህዝቧንም ቤተክርስትያኑንም ታደገች፡፡
እንዲህ ናት የኛ እመቤት ንጽህተ ንጹሐን ቅድስተ ቅዱሣን ንዕድ ክብርት ብጽዕት ድንግል ማርያም!
ጸሎቷና በረከቷ ሁሌም ይጠብቀናል፡፡ እልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልል...
ልመናዋ ክብሯ የልጇም ቸርነት በመላው ሕዝበ ክርስቲያን ላይ ይደር አሜን!!!

Saturday 21 September 2013

ነገረ ቅዱሣን ወቅዱሣት

እንኳን ለሊቀ መላእክት ለቅዱስ ሚካኤል በዓል በሰላም አደረሳችሁ::
የቅዱስ ሚካኤል ምልጃው በረከቱና ፈጣን ተራዳዒነቱ በሁላችን ላይ አድሮ ለዘለዓለም ይኑር!!!

ነገረ ቅዱሣን ወቅዱሣት

እንኳን ለሊቀ መላእክት ለቅዱስ ሚካኤል በዓል በሰላም አደረሳችሁ::
የቅዱስ ሚካኤል ምልጃው በረከቱና ፈጣን ተራዳዒነቱ በሁላችን ላይ አድሮ ለዘለዓለም ይኑር!!!

"የሚካኤል ሠራዊት በየነገዳቸው የገብርኤልም ሠራዊት በየማኅበራቸው፣
ኪሩቤልም በግርማቸው፣ ሱራፌልም በቅዳሴያቸው፣ የመላእክትም
ሠራዊት ሁሉ በየወገናቸው በቅዱሳን ምስጋና የሚመሰገን እግዚአብሔርን ያመሰግኑታል፡፡" 
                                                  /ቅዳሴ ዘቅዱስ ያዕቆብ ኤጲስ ቆጶስ ዘሥሩግ/


ነገረ ቅዱሣን ወቅዱሣት

የቅዱስ ሚካዔል ምልጃና ተራዳዒነት ከክፉ ይጠብቃችሁ...!!!

ነገረ ማርያም

የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ልመናዋ ክብሯ ጣዕሟ በረከቷ የልጇም ቸርነት አይለየን!

ነገረ ማርያም


   
    

ነገረ ቅዱሣን ወቅዱሣት

የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካዔል ምልጃና ተራዳዒነት አይለየን፡፡

ነገረ ማርያም

ወላድተ አምላክ እመቤታችን ንጽህት ብጽዕት ቅድስት ድንግል ማርያም በምልጃዋ ትጠብቀን፡፡

የአባቶቻችንን ፈለግ እንከተል


አስተምህሮተ ቤተ ክርስቲያናችን


Meskel Celebration Live from Meskel Square in Addis Ababa, Ethiopia 2005 E.C

መስቀል አበባ (Meskel Abeba)

ወበዛቲ ዕለት

ልመናዋ ክብሯ የልጇ ቸርነት ከሃገራችን ከኢትዮጵያ ከሕዝበ ክርስቲያን ጋር ጸንቶ ይኑር ለዘለአለሙ አሜን!!!
እንኳን ለእመቤታችን በዓል በሰላምና በጤና አደረሳችሁ አደረሰን አሜን !!!

መስከረም 10 ሥዕለ ጸዴንያ ማርያም 
ጸዴንያ በምትባል ሀገር ማርታ የምትባል ደግ ሴት ነበረች፡፡ ይህች ደግ ሴት በቤቷ ትልቅ አዳራሽ ሰርታ እንግዶችን እንደ አባታችን አብርሃም ተቀብላ አብለታ አጠጥታ ማደሪያ ቦታም ሰጥታ ታስተናግድ ነበር፡፡ አባ ቴዎድሮስ የሚባል ኢትዮጵያዊ መነኩሴ ወደ ኢየሩሳሌም ሲሔድ መሽቶበት ከማርታ ቤት በእንግድነት አድረ ጠዋት ለመሔድ ሲነሣ ወደ ኢየሩሳሌም እንደሚሄድ ሲነግራት የእመቤታችንን ሥዕል ገዝተህ አምጣልኝ ዋጋውን ልስጥህ አለችው፡፡ ገንዘቡን ሥዕሉ ን ሳመጣልሽ ትሰጪኛለሽ ብሏት ሄደ፡፡
ቅዱሳት ቦታዎችን (መካናትን) ተሳልሞ ሥዕሉን ረስቶ ሳይገዛ ሲመለስ « አደራ ጥብቅ አይደለምን? ያቺ ሴት አደራ ያለችህን ለምን ረሳህ» የሚል ድምጽ ሰማ ተመልሶ ሄዶ ገዝቶ በረሃ በረሃውን መጓዝ ጀመረ፡፡ በመንገድም እየተጓዘ አንበሳ ሊበላው አየሮጠ ወደ እሱ ሲመጣበት አየ መነኩሴው አንበሳውን ከመፍራት የተነሣ ደነገጠ ተንቀጠቀጠ ደንግጦ ቁሞ ሳለ ያች ሥዕል ከአንበሳው ጩኸት ሰባት እጅ በሚበልጥ አስፈሪ ድምጽ ጩሃ ተናገረች፡፡ ያን ጊዜ አንበሳው ደንግጦ ፈጥኖ ሸሸ፡፡
መነኩሴውም መንገዱን ቀጠለ፡፡ በመንገዱም ከሚያስፈራ ዱር ውስጥ ወጥተው ወንበዴዎች ሊቀሙትና ሊገድሉት ከበቡት፡፡ ከሥዕለ ማርያሟም እንደ መብረቅ ያለ ታላቅ ቃል ወጣ ፡፡ ወንበዴዎችም እጅግ ፈርተው ሸሽተው ከጫካው ውስጥ ገቡ፡፡
ያም መነኩሴ እኝህን የሚያስደንቁ ተአምራት በሰማና ባየ ጊዜ በልቡ « ለእኔ ረዳት ትሆነኝ ዘንድ ወደ ሀገሬ ይዣት እሄዳለሁ እንጂ ለላከችኝ ሴት አልሰጥም» ብሎ ወደ ሀገሩ ሊሄድ በመርከብ ተሳፈረ፡፡
በባሕር ላይም ሳለ ጽኑ ነፋስ ተነስቶ መርከቡን እየገፋ ማርታ ወዳለችበት ሀገር ወደ ጼዴንያ ዳርቻ አደረሰው፡፡ ማደሪያም ስለሌለው ወደ ደጓ ሴት ወደ ማርታ ቤት ከእንግዶች ጋር አብሮ ገብቶ አደረ፡፡ ሲነጋ ወጥቶ ሊሔድ ከደጃፍ ሲደርስ ደጃፉ ጠፍቶት ከአጥሩ ሲታገል ዋለ፡፡ ማርታም «አባቴ ያመመህ የደከመህ ትመስላለህ ዛሬ ደግሞ እዚህ እደርና ነገ ትሔዳለህ» አለችውና አደረ፡፡ በሁለኛውም ዕለት እንደ መጀመሪያው ቀን በሩን አልፎ መሄድ አቃተውና እዚያው ማርታ ቤት አደረ፡፡ በሦስተኛው ቀን መውጣት ፈልጐ ከአጥሩ ጋር ሲታገል አይታ «አባቴ የሆንከው ምንድነው እነሆ ዛሬ ሦስተኛ ቀንህ ነው፡፡» አለችው፡፡ መነኩሴውም « ይህችን ተአምረኛ ሥዕል አልሰጥም ብዬ ነው፡፡ እኔኮ ሥዕል ከኢየሩሳሌም ግዛልኝ ያልሽኝ መነኩሴ ነኝ» ብሎ ሥዕለ ማርያምን አውጥቶ ሰጣት፡፡ እርሷም እጅግ በጣም ተደስታ እግዚአብሔርን አመሰገነች፡፡ በሥዕሏም ፊት ሰግዳ ለእመቤታችን ለድንግል ማርያም ምስጋናን አቀረበች፡፡
ተቀብላም ሥዕል ቤት አሰርታ በክብር አስቀመጠቻት ይህችም ሥዕል ቅዱስ ሉቃስ የሳላት ናት ሥጋ የለበሰች ትመስላለች፡፡ ከፊቷም ወዝ ይንጠባጠባል፡፡ በዚህችም ሥዕለ ብዙ ተአምራት ተደረገ ሕሙማን ተፈወሱ ዓይነ ስውራን ማየት ቻሉ፡፡
በዚያ ዘመን የነበረው ሊቀ ጳጳስ ተአምሯን ሰምቶ ሥዕሏ ወደ ማርታ ቤት የገባችበት ዕለት መስከረም 10 ቀን እንዲከበር ሥርዓት ሠራ፡፡
እግዚአብሔር አምላክ የእመቤታችንን ፍቅሯን በልቦናችን ጣዕሟን ባንደበታችን ያሳድርብን። አሜን።
ምንጭ፦ የመስከረም አሥር ሰንክሳር እና ተአምረ ማርያም

ወበዛቲ ዕለት

 ወበዛቲ ዕለት ....
የእመቤታችን ተአምር መስከረም ፲ 
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስምበዚች ቀን ጼዴንያ በምትባል አገር ስጋ የለበሰች የምትመስል ስዕል ከሰሌዳዋ ቅባት እየተንጠፈጠፈ አምላክን የወለደች የእመቤታችን የድንግል ማርያም ተአምር ተገለጠ።

ይህቺንም ስዕል የሳላት ወንጌላዊ ሉቃስ ነው። ወደ ጼዴንያ አገርም የመ...ጣችበት ምክንያት አንዲት ስምዋ ማርታ የሚባል መበለት ሴት ነበርችና ቤትዋንም ለእንግዳ ማደሪያ ያደረገች ናት። አምላክን የወለደች እመቤታችን ድንግል ማርያምንም እጅግ ትወዳት ነበር። በሚቻላትም ሁሉ ታገለግላታለች።
በአንዲት ቀንም ስሙ ቴዎድሮስ የሚባል መነኩሴ ከእርስዋ ዘንድ በእንግድነት አደረ። በመልካም አቀባበልም ተቀበለችው። በማግስቱም ስትሸኘው አባት ሆይ የምትሄደው ወዴት ነው? አለችው። እርሱም በከበሩ ቦታዎች ውስጥ ልሰግድ ወደ ኢየሩሳሌም እሔዳለሁ አላት። እርስዋም ከእኔ ገንዘብ ወስደህ የእመቤታችን ማርያምን ስዕል ግዛልኝና በመመለሻህ ጊዜ አምጣልኝ አለችው። እርሱም በራሴ ገንዘብ ገዝቼ አመጣልሻለሁ አላት። ከዚህም በኋላ ኢየሩሳሌም በደረሰ ጊዜ ከቅዱሳት መካናት ተባረከና ሥዕሏን ሳይገዛ ወደ ጐዳናው ተመለሰ። ያን ጊዜም ሥዕል መግዛት ህን ለምን ረሳህ የሚል የሚያስደነግጥ ድምጽ ሰማ።

ወደ ገበያም ተመልሶ ላሕይዋና መልኳ ያማረና የተወደደ የሆነ የእመቤታችን ማርያምን ሥዕል አግኝቶ ገዛት። በሐርና በንጹሕ ልብስም ጠቀለላት።
በጐዳናውም እየተጓዘ ሳለ ከሚያስፈራ ዱር ውስጥ ወንበዴዎች ተነሱበት ሊሸስም ወደደ ከዚያችም ሥዕል መንገድህን ሒድ የሚል ቃል ወጣ የተከተለውም ሳይኖር መንገዱን ተጓዘ። ሁለተኛም ነጥቆ ሊበላው አንበሳ ተነሣ ያን ጊዜም ከዚያች ሥዕል የሚያስፈራ ድምጽ ወጥቶ አንበሳውን አባረረው።
አባ ቴዎድሮስም ይሄነን ሁሉ ድንቅ ተአምር በአየ ጊዜ ያቺን ሥዕል ወደ አገሩ ሊወስዳት ወደደ ።ግዛልኝ ላለችው መበለት ይሰጣት ዘንድ አልፈለገም።
ከዚህም በኋላ በመርከብ ተሳፍሮ በሌላ አቅጣጫ ሲጓዝ ታላቅ ንፋስ ተነሣበት ወደ ማርታ አገር ወደ ጼዴንያም ወሰደው። ከመርከብም ወርዶ ከብዙ ፡ አንግዶች ፡ ጋር ወደዚያች መበለት ቤት ሄደ። ማንነቱንም አልገለጸላትም። እርሷም አላወቀችውም።

በማግስቱም ተሠውሮ ወጥቶ ወደ አገሩ ሊሔድ በፈለገ ጊዜም የቅጽሩን ደጃፍ አጥቶ ሲያጥመሰምስ ዋለ። በመሸም ጊዜ ወደ ማደርያው ተመለሰ። አንዲህ ሆኖ እስከ ሦስት ቀን ኖረ። በመሸ ጊዜ በሩን ያየዋል። ነግቶ መሔድን ሲሻ የበሩ መንገድ ይሠወረዋል። ያቺም መበለት አባቴ ሆይ አእምሮህ ተነክቷልን? ስትቅበዘበዝ አይሃለሁና ምን ሁነህ ነው? አለችው። ከዚህም በኋላ ከዚያች ሥዕል የሆነውን ሁሉ ነገራት። ራሱንም ገለጠላት። ያቺንም ሥዕል ሰጣት። ተቀብላም የተጠቀለለችበትን ልብስ ስትፈታ ፈሳሽ ወዝ ከስዕሊቱ ሲንጠፈጠፍ አገኘች። ከደስታዋም ብዛት የተነሣ የዚያን መነኩሴ እጆቹንና እግሮቹን ሳመች። ከዚህም በኋላ ያቺን ሥዕል ወደ ጸሎት ቤቷ ወስዳ በታላቅ ክብር የምትቀመጥበትን አዘጋጅታ አኖረቻት ማንም እንዳይዳስሳትም የነሐስን መስኮትን ሰራችላት። በሌሊት የሚያበሩ መቅረዞችን በፊቷ ሰቀለች። ከመቅረዞችም ውጭ የሐር ፡ መጋረጃን ጋረደች ከሥዕሊቱ እየተንጠፈጠፈ የሚወርደው የወዝ ቅባት የሚጠራቀምበት ከዕብነ በረድ የተሰራ ወጭት አኖረች። ያም መነኮስ እስከሚሞትበት ቀን ፡ ድረስ ፡ የእመቤታችንን ድንግል ማርያምን ሥዕል እያገለገለ ኖረ።
የሀገሩም ሊቀ ጳጳሳት የዚያችን ሥዕል ዜና በሰማ ጊዜ ከኤጲስቆጶሳትና ከካህናት ከሕዝቡም ሁሉ ጋር መጣ በሠሌዳም ውስጥ ሆና አገኙዋት ከዚህ ከአምላካዊ ግብር የተነሣ አደነቁ። ከዚያም ቅባት ቀድተው ለበረከት በተካፈሉ ጊዜ ወዲያውኑ በውጭቱ ውስጥ ይሞላል። ወደ ሌላ ቦታ ሊወስዷት በፈለጉ ጊዜ ንውጽውጽታ ሁኖ ብዙዎች በድንጋጤ ወደቁ ሥዕሊቱም እስከ ዛሬ በዚያች አገር ትኖራለች።
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን!!!
እኛንም በእናቱ በድንግል ማርያም ጸሎት ይማረን!!!

ጊሸን ደብረ ከርቤ

እሠይ ሥለቴ ሠመረ (2)
ለጊሸን ማርያም ነግሬያት ነበረ፡፡...
አልጋ በአልጋ ነው መንገዱ፣
ጊሸን ማርያም ሲሔዱ፡፡... እልልልልልልልልልልልልልልልልልልልል
የቃል ኪዳኗን በረከት ያዲላችሁ::

ጊሸን ደብረ ከርቤ

የጊሸን ደብረ ከርቤ ዳግማዊት ኢየሩሣሌም ረዲኤትና በረከት ተካፋይ ያድርጋችሁ፡፡
የእግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስቲያን፡፡